በዚሁ አዋጅ መሠረት ለቢሮው ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የክልሉን መንግስት በጀት ማዘጋጀት፣ በተፈቀደው በጀት መሠረት ክፍያ መፈጸም፣ የበጀቱን አፈጻጸም ማስተዳደር፣ መገምገምና መቆጣጠር፤ የክልሉ መንግስት የበጀት፣የሂሳብ፣የክፍያና የውስጥ ኦዲት ሥራዓት መዘርጋትና በስራ ላይ እንዲውል ማድረግና መከታተል፤ የክልሉን መንግስት የገንዘብ ሰነዶች፣ ገንዘቦችና ንብረቶች መያዝና ማስተዳደር ይገኙበታል፡፡ ከአጋር ድርጅቶች የሚገኝ ሀብት በውጤታማና በተቀላጠፈ አኳን ለማስተዳደርም የክልሉ መንግስት የብድርና እርዳታ ስምምነቶችን መፈራረምና ማስተዳደር፤ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጉዳዮችን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ማስተባበርና መቆጣጠር፤ ለሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች የቅድመ ስምሪት የስራ ውል ፈቃድ መስጠት፤ የሲቪል ማህበረሰብ ፕሮጀክቶችን የማበልጸግ /Project Appraisal/፣የመጽደቅና የመፈራረም ሂደትን የመምራትና የማስተባበር፤አተገባበራቸውንም በመስክ የመከታታልና መገምገም ሥራዎች ይገኙበታል፡፡
እንዲሁም ዘመናዊ የበጀት አስተዳደር፤ የሂሳብ አያያዝ፣ የግዥና የንብረት አስተዳደር ስርዓት መመስረት፣በስራ ላይ መዋሉን መከታተልና መቆጣጠር፤ የክልሉን መንግስት የፋይናንስና ንብረት ኢንስፔክሽን ማከናወን፣ እርምጃ መውሰድና እንድወስድ ማድረግ፤ የክልሉን መንግስት የገቢ ደረስኝ ማሳተም፣ ማሰራጨት፣መከታተልና መቆጣጠር፤ በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን እንቅስቃሴና ተግባራት መከታተል፣ መቆጣጠርና አፈጻጸሞችን መገምገም እንዲሁም ዓላማውን ለመፈጸም የሚረዱ ሌሎች ሥራዎችን ማከናወን ተግባራቶች ይገኙበታል፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን ሥልጣንና ተግባራትን በብቃትና በላቀ ደረጃ ለመፈጸም እንዲችል ለማድረግ ለቢሮ ተጠሪ የሆኑ ኤጀንሲና ባለስልጣን መ/ቤቶችን ጨምሮ በአራት ዘርፎች ማለትም አስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ፣ የመንግስት ፋይናንስ አሰተዳደር ዘርፍ፣የኢንስፔክሽንና የውስጥ ኦዲት ዘርፍ እና የፊሲካል ፖሊሲ፣የሲቪክና ትብብር ዘርፍ በማዋቀር በስራቸውም የተለያዩ ተግባራት ሊያከናውኑ የሚችሉ ዳይሬክቶሬችን እንዲቋቋሙ በማድረግ የሚያከናውኑትን ተግባራትና ድርጀታዊ መዋቅር በማደረጀት ተዘጋጅቶ ቀርቦኣል፣