Services Of Bureau

Download Brochures

Our Office

address: Beside of Hawassa City Primary Court

phone (+251) 13181046

Email : snrsbof@snrsfb.gov.et

Fax(046)-220-60-84        

PostP.S.K. 485

በየዘርፉና ዳይሬክቶሬቶች የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

                     የመንግስት ፋይናንስ አሰተዳደር ዘርፍ
በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ዉስጥ ከሚገኙ ዘርፎች አንዱ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ዘርፍ ነዉ፡፡ መንግሥት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች በገንዘብ ወይም በዓይነት የሚሰበሰብ ሀብት ለመንግሥት መደበኛና ካፒታል ሥራዎች  ለሚያደረገዉ እንቅስቃሴ ወጪዎችን መሸፈንን፣ ማስተዳደር እና መቆጣጠርን አካቶ የሚመራ የሥራ ዘርፍ ነዉ፣  ከክልል እስከ ወረዳ/ቀበሌ ድረስ የመንግሥት ሀብት የሚመረባቸዉ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀትና በማፀደቅ ለክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶችና ለአስተዳደር እርከኖች በማሰራጨት ሥራ ላይ እንዲዉል ከማድረግም አንፃር ተግባራትን የሚያከናወን ነዉ፡፡ የተፈቀደዉን በጀት፣ የተላለፈዉን ጥሬ ገንዘብ፣ የተከፈለዉን ክፍያ፣ በሥራ ላይ የዋለዉን ሀብት፣ የሀብትና የዕዳ፣  የገቢና የወጪ ፋይናንሻል ሪፖርቶችና መገለጫዎችን በማዘጋጀት ለሚመለከታቸዉ አካላት በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ተደራሽ በማድረግ አፈጻጸሙን በዉስጥና በዉጭ ኦዲተሮች እንዲመረመር ያደርጋል፡፡ በተገኙት ኦዲት ግኝቶችም ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ ግብረ መልስ ይሰጠል፡፡ በዘርፉ የተሟላ የሰዉ ኃይል እንዲሟላ በማድረግ የዘርፉ ባለሙያዎችንና የአመራር አካላት የክህሎት ክፍተት በመለየት የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት የዘርፉ ሥራዎች ዉጤታማ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃርም ሚናዉ ከፍተኛ ነዉ፡፡
በአዋጁ ለዘርፉ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት በስሩ ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ  በተደራጁት ዳይሬክቶሬቶቹ አማካይነት ክልላዊና የየአሰተዳደር እርከኑን ዘመናዊ የበጀት አስተዳደር፣ የሂሳብ አያያዝ፣ በስራ ላይ መዋሉን መከታተልና መቆጣጠር፤ ማሰራጨት፣መከታተልና መቆጣጠር፤ እንዲሁም ዓላማውን ለመፈጸም የሚረዱ ሌሎች ሥራዎችን ለማከናወን እንዲያስችለው ዘርፉ በአራት ዳይሬክቶሬት የተከፋፈሎ ተግባራትን ይመራል፡፡ የዳይሬክቶሬቶቹ ኃላፊነትና ተግባራት ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርቧል፡፡

የመንግሥት ሂሳብ ማጠቃለያ ዳይሬክቶሬት

ዳይሬክቶሬቱ ከዘርፉ ዓላማ በመነሰት የዳይሬክቶሬቱን ሥራዎች በማቀድ፣ በመምራትና በማስተባበር የመንግሥት ሂሳብ አያያዝ ሥረዓት በማስተገበር፣ በማገምገምና በማሻሻል የመንግሥት ሂሳቦች በወቅቱ  እንዲቀርቡ፣ እንዲጠቃላሉ እና እንዲዘጉ በማድረግና በማስመርመር እንዲሁም የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በመስጠት፣ በመከታተል እና በመደገፍ ዘመናዊ የመንግሥት ሂሳብ አያያዝና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር ያደርጋል፡፡

በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የዘርፎችና ዳይሬክቶሬቶች አደረጃጀት

የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ዘርፍ
በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ዉስጥ ከሚገኙ ዘርፎች አንዱ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ዘርፍ ነዉ፡፡ መንግሥት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች በገንዘብ ወይም በዓይነት የሚሰበሰብ ሀብት ለመንግሥት መደበኛና ካፒታል ሥራዎች  ለሚያደረገዉ እንቅስቃሴ ወጪዎችን መሸፈንን፣ ማስተዳደር እና መቆጣጠርን አካቶ የሚመራ የሥራ ዘርፍ ነዉ፣  ከክልል እስከ ወረዳ/ቀበሌ ድረስ የመንግሥት ሀብት የሚመረባቸዉ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር የህግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀትና በማፀደቅ ለክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶችና ለአስተዳደር እርከኖች በማሰራጨት ሥራ ላይ እንዲዉል ከማድረግም አንፃር ተግባራትን የሚያከናወን ነዉ፡፡ የተፈቀደዉን በጀት፣ የተላለፈዉን ጥሬ ገንዘብ፣ የተከፈለዉን ክፍያ፣ በሥራ ላይ የዋለዉን ሀብት፣ የሀብትና የዕዳ፣  የገቢና የወጪ ፋይናንሻል ሪፖርቶችና መገለጫዎችን በማዘጋጀት ለሚመለከታቸዉ አካላት በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ተደራሽ በማድረግ አፈጻጸሙን በዉስጥና በዉጭ ኦዲተሮች እንዲመረመር ያደርጋል፡፡ በተገኙት ኦዲት ግኝቶችም ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ ግብረ መልስ ይሰጠል፡፡ በዘርፉ የተሟላ የሰዉ ኃይል እንዲሟላ በማድረግ የዘርፉ ባለሙያዎችንና የአመራር አካላት የክህሎት ክፍተት በመለየት የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት የዘርፉ ሥራዎች ዉጤታማ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃርም ሚናዉ ከፍተኛ ነዉ፡፡
በአዋጁ ለዘርፉ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት በስሩ ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ  በተደራጁት ዳይሬክቶሬቶቹ አማካይነት ክልላዊና የየአሰተዳደር እርከኑን ዘመናዊ የበጀት አስተዳደር፣ የሂሳብ አያያዝ፣ በስራ ላይ መዋሉን መከታተልና መቆጣጠር፤ ማሰራጨት፣መከታተልና መቆጣጠር፤ እንዲሁም ዓላማውን ለመፈጸም የሚረዱ ሌሎች ሥራዎችን ለማከናወን እንዲያስችለው ዘርፉ በአራት ዳይሬክቶሬት የተከፋፈሎ ተግባራትን ይመራል፡፡ የዳይሬክቶሬቶቹ ኃላፊነትና ተግባራት ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርቧል፡፡
  1. የትሬዤር ዳይሬክቶሬት
  • የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
  • በክልሉ ምክር ቤት የፀደቀዉን ዓመታዊ በጀት መነሻ በማድረግ በመደበኛና በካፒታል፣ በደመወዝና በሥራ ማስኬጃ በመለየት  በክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶችና በክልለ ተቋማት ሥር በሚገኙ የስራ ክፍሎች፣ በዞኖች፣ በልዩ ወረዳዎች፣ በወረዳዎች እና በከተማ አስተዳደር ስም የበጀት መረጃ ለይቶ በመያዝ ይቆጣጠራል፣
  • ለዓመቱ የተፈቀደዉን በጀት መነሻ በማድረግ ከፌዴራል የሚገኝ ድጎማ ገቢ፣ ከክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች፣ ከከልል ተቋማት፣ ከዞኖች፣ ከልዩ ወረዳ፣ ከወረዳ እና ከከተማ አስተዳደር  ለመሰብሳብ በዕቅድ የተያዘዉን መረጃ አደራጅቶ በመያዝ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
  • ከሁሉም የአስተዳደር እርከኖች የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት በመሰብሰብ ዓመታዊ የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር በማዘጋጀት ለፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ያቀርባል፣
  • ከክልሉ ለፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር በቀረበዉ ጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር መሠረት የድጎማ በጀት ወይም ገቢ በወቅቱ መላኩን ይከታተላል፣
  • የክልል ቢሮዎች የሚያቀርቡትን የክፍያ ጥያቄ በመቀበል ከተፈቀደላቸዉ በጀትና የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር መሠረት የቀረበ መሆኑን በማጣራት የባንክ ጣሪያ ይመሰርታል፣
  • የክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች የተሰጣቸዉን የባንክ ጣሪያ መነሻ በማድረግ ከፍያ መፈፀማቸዉንና ከማዕካለዊ ግምጃ ቤት በጥሬ ገንዘብ መተካቱን ያረጋግጣል፣
  • ከሁሉም አስተዳደር እርከኖች ተንከበላይ የ3 ወራት የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ በማድረግ በቀረበዉ መርሃ ግብር መሠረት ይፈፅማል፣
  • በየወሩ ለዞኖች፣ ለልዩ ወረዳዎች፣ ለወረዳዎች እና ለከተማ አስተዳደሮች የቀረበዉን የጥሬ ገንዘብ ፋላጎት መርሃ ግብርና የተፈቀደላቸዉን በጀት መነሻ በማድረግ የባንክ ማዛዣ ደብደቤ በማዘጋጀት የጥሬ ገንዘብ ዝዉዉር ይፈጽማል፣
  • ለክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች፣ ለክልል ተቋማት፣ ለዞኖች፣ ለልዩ ወረዳዎች፣ ለወረዳዎች እና ለከተማ አስተዳደሮች የደመወዝ ገንዘብ ሲተላለፍ የሲቪል ሠራተኞችና የሚሊተሪ የሠራተኞችና የመንግሥት የጡረታ መዋጮ ድርሻ ከሚተላለፈዉ ገንዘብ ቀንሶ በማስቀራት በየወሩ ለብሔራዊ ባንክ ያስተላልፋል፣
  • የመንግሥት ገንዘብ በታለመለት ዓላማ ላይ ዉጤታማ በሆነ መንገድ እንዲዉል ለማድረግ ዘመናዊ የመንግሥት የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ሥርዓት በየደረጃዉ ወጥነት ባለዉ መንገድ እንዲዘረጋ ያደርጋል፣
  • በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሳጥን የሚያዝ የጥሬ ገንዘብ ጣሪያ በመወሰን በዉሳኔዉ መሠረት እንዲተገበር ያደርጋል፣
  • የክልሉ የተጠቃለለ ፈንድ አካዉንት ሂሳብ መቆጣጠርና ማስተዳደር፣
  • የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የባንክ ሂሳቦችን መክፈት፣ መቆጣጠር፣ ማስተዳደር እና የማይቀሰቀሱ የባንክ ሂሳቦችን ይዘጋል፣
  • በአመታዊና በተንከበላይ የ3 ወር የጥሬ ገንዘብ ፋላጎት መርሃ ግብር መሠረት ይገኛል ተብሎ በዕቅድ የተያዘ ገንዘብ፣ የተከፈለዉ እና ከወጪ ቀሪ የገንዘብ ሚዛን የሚያሳይ የገቢና የወጪ መግለጫ አዘጋጅቶ በመገምገም የአፈፃፀሙ ሪፖርቱን ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀርባል፣
  • በክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች ዜሮ ሚዛን የክፍያ ሥርዓትን በማሻሻል ዘመናዊ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት ሥርዓት ይዘረጋል፣
  • በዞንና በወረዳ የሚተገበረዉን አንድ የፋይናንስ የጋራ አገልግሎት(ፑል) ክፍያ ሥርዓት በመገምገም የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም ወቅቱ የሚፈልገዉን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የአሰራር ሥርዓቱን ዘመናዊ እንዲሆን ያደርጋል፣
  • ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፈሰስ ሂሳቦች በወቅቱ ወደ ማዕከላዊ ግምጃ ቤት ገቢ እንዲሆን ያደርጋል፣
  • በክፍያ አፈጻጸም ላይ ክፍተት ያለባቸዉን የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን በመለየት የድጋፍና የክትትል ሥራዎችን በማከናወን ግብረ መልስ ይሰጣል፣
  • የአቅም ግንባታ ክፍተቶችን በመለየት በክፍያ አፈጻጸም ዙሪያ የሚታዩ የአፈጻጸም ችግሮችን በመለየት የሥልጠና ሰነድ አዘጋጅቶ ሥልጠና ይሰጣል፣
  • በቢሮ በሚዘጋጁ የዉይይት መድረኮች ላይ በመገኘት በክፍያና በጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ዙሪያ በሚነሳ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ይሰጣል፣
  • የጥሬ ገንዘብ አስተዳደርና የክፍያ አሰራር ሥርዓትን በተመለከተ የሚፈለጉ መረጃዎችን አደራጅቶ ለገንዘብ ሚኒስቴርና ለሌሎችም አካላት ያቀርባል፣
  • በሁሉም አስተዳደር እርከን በጥሬ ገንዘብ አስተዳደርና አጠቃቀም ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በጥናት በመለየት ችግሮቹን በዘላቂነት እንዲፈታ ያደርጋል፣
  • ከእንስፔክሽንና ከዉስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ጋር በማቀናጀት አለአግባብ የተከፈሉ ክፍያዎች ተመላሽ ሆነዉ ወደ ማዕከላዊ ግምጃ ቤት ገቢ እንዲሆን ያደርጋል፣
  • የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና የአሰራር ማንዋሎች ሲዘጋጁ የጥሬ ገንዘብ አስተዳደርና የክፍያ አሰራር ሥርዓትን በተመለከተ አሰራር ሥርዓትን ዉጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ ሀሳቦችን ያቀርባል፣
  • የመንግሥት ገቢ የሚሰበሰብባቸዉ የገቢ ደረሰኞች በጥንቃቄ እንዲጠበቁ ክትትል ያደርጋል፣
  • የመንግሥት ገንዘብ ክፍያ የሚፈጸምባቸዉ የሂሳብ ሰነዶችና ቼኮች በአግባቡ እንዲጠበቁ ያደርጋል፣
  • ክፍያ የተፈጸመባቸዉ የክፍያ ሰነዶች በወቅቱ በተቀናጀ በፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ቋት(IBEX) እንዲመዘገቡ ለሂሳብና ሪፖርት ማጠቃለያ ዳይሬክቶሬት በየዕለቱ ያስተላልፋል፣
  • በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
  • በዳይሬክቴሩ የሚያስፈልጉ የሥራ ቁሳቁሶች እንዲሟላ ያደርጋል፣
  • በቢሮ የዳይሬክቶሬቱ መዋቅር ሲዘጋጅ አስፈላጊዉን ግብዓቶችን በማቅረብ አብሮ ያዘጋጃል፣
  1. የመንግስተ ሂሳብ ማጠቃለያ ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክቶሬቱ ከዘርፉ ዓላማ በመነሰት የዳይሬክቶሬቱን ሥራዎች በማቀድ፣ በመምራትና በማስተባበር የመንግሥት ሂሳብ አያያዝ ሥረዓት በማስተገበር፣ በማገምገምና በማሻሻል የመንግሥት ሂሳቦች በወቅቱ  እንዲቀርቡ፣ እንዲጠቃላሉ እና እንዲዘጉ በማድረግና በማስመርመር እንዲሁም የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በመስጠት፣ በመከታተል እና በመደገፍ ዘመናዊ የመንግሥት ሂሳብ አያያዝና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር ያደርጋል፡፡
  • አለም አቀፍ ይዘት ያለዉ የተቀናጀ ዘመናዊ የፋይናንስ መረጃ አያያዝ ሥርዓትን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እንዲዘረጋና እንዲተገበር ማስተባበር፣ መከታተል፣ መደጋገፍና ማስፈፀም፣
  • የመንግሥት ሂሳብ አያያዝ ሥርዓት የተቀመጠዉን ስታንዳርዱን ተከትሎ እንዲፈፀም የአሰራር ሥርዓት ሊያሳዩ የሚችሉ ማንዋሎች እንዲዘጋጁ ማድረግ፣
  • የመንግሥት ሂሳብ አሰራር ሥርዓት እንዲሻሻል የተለያዩ ጥናቶች እንዲካሄዱ በማድረግ በሚቀርቡ ጥናቶችን ላይ ቴክኒካዊ ግምገማዎችን በማካሄድ አሰራር ሥርዓቱን ወቅታዊ ያደርጋል፣
  • የአገር አቀፍ ደረጃዎችን ልያሟሉ የሚችሉ የሂሳብ ሙያ መለኪያዎች(Accounting Standards) ተጠንቶ ሲቀርቡ ከበላይ ኃላፊዎች ጋር በማነጋገር  በሥራ ላይ እንዲዉል ሲወሰን ለክልሉ ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች፣ ለዞኖች፣ ለልዩ ወረዳዎች፣ ለወረዳዎች እና ለከተማ አስተዳደሮች የተሸሻሉ ሰነዶች በማሰራጨት በሥራ ላይ መዋላቸዉን ይከታተላል፣
  • የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ሥርዓት የሚመራባቸዉ መመሪያዎችና የአሰራር ማንዋሎችን ተዘጋጅቶ እንዲተገበሩ ማድረግና አፈጻጸማቸዉን ይከታተላል፣
  • በፌዴራል እንዲሁም በሌሎች ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ደረጃ የተቀመሩ የመንግሥት ሂሳብ አያያዝ ምርጥ ተሞክሮ ዘዴዎችን በመዉሰድ ወደ ተግባር እንዲለወጥ ያደርጋል፣
  • በመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ሥር የሚገኙ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የሥልጠና የዳሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ በጥናቱ ዉጤት መሠረት የሥልጠና ሰነድ ማዘጋጀት፣
  • ከመንግሥት ሂሳብ አያያዝ ሥራዎች ጋር በተያያዘ ለሚዘጋጁ የመሥሪያ ቤቱ አዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያዎች በጥናት የተደገፈ ግብዓቶችን መስጠትና ሲፀድቅም በሥራ ላይ ማዋሉን ይከታተላል፣
  • ከትሬዥሪ ዳይሬክቶሬት የሚቀርቡ ሰነዶችን መሠረት በማድረግ የየቀኑን የወጪና ገቢ ሂሳቦች እንቅስቃሴ መመዝገብ፣ ማዋራረስ፣ ወቅታዊ የሆነዉን የሂሳብ መረጃዎችን መነሻ በማድረግ ወቅታዊ የሂሳብ ሪፖርቶችና በማዘጋጀት ለሚመለከታቸዉ አካላት ሁሉ ተደራሽ ማድረግ፣
  • የሂሳብ እንቅስቃሴዎች በተፈቀደላቸዉ የሂሳብ መደቦች አቅጣጫዎችን ጠብቆ እንዲመዘገቡ ያደርጋል
  • ሂሳቦች በየወሩ በተፈቀደላቸዉ ሂሳብ አቅጣጫዎች መሠረት ሚዛናቸዉ በትክክል እንዲታረቁ ያደርጋል፣
  • የክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶችና ተቋማት ጥሬ ገንዘብ ያልሆኑ (Non Cash Transaction) የፈሰስ ሂሳቦች ተቀብሎ ይመዘግባል፣
  • የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ወርሃዊ የሂሳብ ሪፖርቶች(የገቢ፣ የወጪ፣ የተሰብሳቢ፣ የተከፋይ፣ የዝዉዉር እና የሂሳብ ማመዛዘኛ) በተቀናጀዉ ዘመናዊ የፋይናስ መረጃ ሥርዓት በትክክል መመዝገባቸዉንና መታረቃቸዉን በማረጋገጥ ግብረ መልስ ይሰጣል፣
  • የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የባንክ ማስታረቂያና የጥሬ ገንዘብ ቆጠራ ሰርተፍኬት በትክክል እንዲዘጋጅና ለዳይሬክቶሬቱ እንዲቀርብ ያደርጋል፣
  • የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተከፋይና የተሰብሳቢ ሂሳቦች በዕድሜ ዘመን(Aging Analisis) ለይቶዉ መዝግቦ እንዲያቀርቡና የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ ሚዛናቸዉ እንዲቀንስ ያደርጋል፣
  • የመንግሥት ገቢና ወጪ፣ የተፈቀደ በጀትና ወጪ፣ የሀብትና የዕዳ ዓመታዊ መግለጫዎች በማዘጋጀት ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀርባል፣
  • የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ያቀረቡት የበጀት፣ የገቢ፣ የወጪ፣ የተሰብሳቢ፣ የተከፋይ እና የዝዉዉር ሂሳቦችን ወቅታዊነት በማረጋገጥ ከተፈቀዱ በጀት ምንጮች ጋር የሚታረቅ መሆኑን ያረጋግጣል፣
  • የተሰብሳቢና የተከፋይ ሂሳቦች መሰብሰብና መክፈል የማይችሉ መሆናቸዉን በመለየት ከመዝገብ እንዲሰረዝ በደንቡና በመመሪያ መሠረት መረጃ እንዲደራጅ በማድረግ ለዉስጥና ለወጪ ኦዲተሮች እንዲቀርብ ያደርጋል፣
  • የተጠቃለሉ የሂሳብ ሪፖርቶችን በመዝጋት በሃርድና በሶፍት ኮፒ እንዲደራጅ በማድረግ ለዉስጥና ለዉጭ ኦዲተሮች በማቅረብ እንዲመረመር ያደርጋል፣
  • የወስጥና የዉጭ ኦዲተሮች ለሚጠይቁት ጥያቁዎች ማብራሪያ ይሰጣል፣
  • በኦዲት ግኝቶች ላይ የኦዲት ማጠቃለያ የመዉጫ ስብሰባ(Exit Conference) የመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊዎች በተገኙበት ለሚነሱ ለኦዲት ጉዳዮች ምላሽ ይሰጣል፣
  • ኦዲት የተደረጉና የተጠቃለለ የመንግሥት ሂሳብ ሪፖርት ለዜጎች፣ ለልማት አጋሮች እና ለልዩ ልዩ ተጠቃሚ አካላት እንዲጠቀሙበትና እንዲያወቁት ያደርጋል
  • በተገኙት ኦዲት ግኝቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ ግብረ መልሱን ለሚመለከታዉ አካላት ያቀርባል፣
  • በየበጀት ዓመቱ ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሚሰጡ ኦዲት አስተያየቶች የማስተካከያ እርምጃ ለመዉሰድ የሚያስችሉ የድርግት መርሃ ግብር ማቅረቢያ ቼክሊስት በማዘጋጀት በመከታተል በኦዲት ግኝቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃ መዉሰዳቸዉን ያረጋግጣል፣
  • ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸዉን የክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች፣ ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎች፣ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች በመለየት፣ የተለዩ ችግሮች ማስተካከል የሚያስችሉ ቼክ ሊስት በማዘጋጀት ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ አፈጻጸሙን መከታተልና ግብረ መልስ ይሰጣል፣
  • በክልል ባለበጀት መ/ቤቶች፣ በዞኖች፣ በልዩ ወረዳዎች፣ በወረዳዎች እና በከተማ አስተዳደሮች ዉስጥ ለረጅም ጊዜ ሲንከባለሉ የመጡ ያልተወራረዱና ሊወራረዱ የማይችሉ ተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦች በዕድሜ ዘመን መረጃዉ ተዘጋጅቶ በአግባቡ መያዛቸዉን ያረጋግጣል፤
  • ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና ተቋማት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በመንግሥት ሂሳብ አያያዝ ሥርዓት ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችና በመስጠት የሥልጠና ፋይዳዉን ይፈትሻል፣የስልጣናውን ዉጤታማነት ዳሰሳ ጥናት ያደርጋል፤
  • ወርሃዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የስድስት ወር፣ የዘጠኝ ወር እና ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታቸዉ አካላት በመስጠት በሚሰጠዉ ግብረ መልስ መሠረት የማስተካከያ እርምጃ መዉሰድና ስለመወሰዱ ይከታተላል፤
  • የዳይሬክቶሬቱን ዓላማ ለማሳካት የሚያስፈልገዉ የሰዉ ኃይልና የሥራ ግብዓቶች እንዲሟላ ያደርጋል
  • በዳይሬክቶሬቱ ሥራ ለተመደቡ ባለሙያዎች እንደየደረጃቸዉ ዝርዝር የሥራ ድርሻ በመስጠት በቅርበት በመከታተልና በመገምገም አፈጻጸማቸዉን በመሙላት ግብረ መልስ ይሰጣል፣
  • የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች ክፍተት በመለየት ባለሙያዎች ሥልጠናና ግንዛቤ እንዲያገኙ ያደርጋል፣
  • ዳይሬክቶሬቱን በሚመለከቱ በተለያዩ ስብሰባዎች፣ሴሚናሮች ላይ በመገኘት የልምድ ልዉዉጦችንና ግንዛቤ በመቀመር በዳይሬክቶሬት ሥር የሚገኙ ባለሙያዎችን ዉጤታማ የሆነ ሥራ እንዲያከናወኑ ማድረግ፣የተገልጋዮችን እርካታ ደሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የሚሻሻልበት ሁኔታ ይቀይሳል፣
  • በቢሮ ዳይሬክቶሬቱን በሚመለከት የመዋቅር ጥናት የሚደረግ ከሆነ አስፈላጊዉን ግብዓቶችን በማቅረብ ባለሙያዎች እንዲሰተፉ ያደርጋል፣
  • በየዕለቱ በተቀናጀዉ በመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር የመረጃ ቋት ሂሳቦችን ለመመዝገብ ከትሬዠሪ ዳይሬክቶሬት የሂሳብ ሰነዶችን ዝርዝር ይረከባል
  • በቀረቡት የሂሳብ ሰነዶች መሠረት የሂሳቦች ጥራት በመጠበቅ ምዝገባ ማካሄድ፣
  • ሂሳቦች ከተመዘገቡ በኃለ የሂሳብ ሰነዶችን በመሄ 42 በዝርዝር በመመዝገብ ለሰነድ ያዥ ያስረክባል፣
  • የሂሳብ ሰነዶች በሰነድ ክፍል መረጃ ፈላጊዎች በቀላሉ መገኘት በሚችሉበት ሁኔታ በየዓመቱ በየወሩ እና በቀን ተለይቶ እንዲደራጁ ያደርጋል፣
  • ለሰነድ አያያዝና አጠባበቅ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ቁሳቁሶች እንዲሟሉ ያደርጋል፣
  • የሰነድ አያያዝና አጠባበቅ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ያደርጋል፣
  • ኦዲት ተደርጎ ከ10 ዓመት በላይ ከቆዩ ከሂሳብ ሰነዶች በፍርድ ቤት የሚፈለጉትን በመለየት እንዲወገዱ ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀርባል፡፡
የመንግሥት ሂሳብና ሪፖርት ማጠቃለያ ዳይሬክቶሬት በሥሩ ሁለት ቡድኖች አሉት
  • የሂሳብ ማጠቃለያ ቡድን 
  • በዚህ ቡድን ክፍያ የተከፈለባቸዉና ገቢ የተሰበሰበባቸዉ የሂሰብ ሰነዶችን መነሻ በማድረግ በየዕለቱ በተቀናጀ በበጀትና በወጪ ሶፍት ዌሪ(IBEX) የገቢ፣ የወጪ፣ የዝዉዉር፣ የተስብሳቢ፣ የተከፋይ እና ሌሎች የማስተካከያ ሂሳቦችን ይመዘግባል፣
  • የክልል ቢሮዎች፣ የክልል ተቋማት፣ የአስተዳደር እርከኖች በየወሩ የሂሰብ ሪፖርቶችን በስታንደርዱ መሠረት መምጣቱን አጣርቶ ይቀበላል፡፡
  • ከሂሳብ ምዝገባ እስከ ሂሳብ ማዘጋጀት፣ ማጠቃላል እና መዝጋት ድረስ ያለዉን ተግባራት በሙሉ ያከናወናል፡፡
  • ከምዝገባ በኃለ የሂሰብ ሰነዶችን ወደ ሰነድ ክፍል ያስተላልፋል፡፡
  • የበጀት ጣሪያና የሂሳብ መረጃ ጥራት ክትትል ቡድን
  • ክፍያ የተፈፀማዉ ወጪ/ክፍያ በተፈቀደዉ በጀት መሠረት መሆኑን ያጣራል፣
  • በጀት ባልተፈቀደበት ለተከፈሉ ክፍያዎች የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
  • ከተፈቀደዉ በጀት በላይ በተከፈሉ ክፍያዎች ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
  • ከተፈቀደዉ የፋይናንስ ምንጭ ዉጪ የተመዘገቡ ሂሳቦችን በመለየት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
  • የተሰብሳቢ ሂሳቦች በዕድሜ ዘመናቸዉ መመዝገባቸዉን በማጠራት በወቅቱ ማወዳደቃቸዉን ይከታተላል፣
  • ረጅም ዘመናት ባለቤት የሌላቸዉን ተሰብሳቢ ሂሳቦች የተቀመጠዉን የአሰራር ሥርዓት ተከትሎ ከመዝገብ እንዲዘረዝ ለሚመለከታቸዉ አካላት ዝርዝር መረጃ እንዲቀርብ ያደርጋል፡፡
  • በየጊዜ የተሰብሳቢ ሂሳቦች እንቅስቃሴ በመከታተልና በመገምገም ሚዛኑ እንዳይከማች ቼክሊስት አዘጋጅቶ ክትትል በማድረግ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
  • ተከፋይ ሂሳቦች በዕድሜ ዘመናቸዉ በዝርዝር ተመዘግቦ ማቅረቡን በማጠራት በወቅቱ ለሚመለከታቸዉ አካላት ዕዳዉ በወቅቱ እንዲተላለፍ ይከታተላል፣
  • በተስብሳቢና በተከፋይ ሂሳቦች መረጃ ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ማሻሻያ መኖሩን ለማረጋገጥ
መረጃዎችን ከIBEX በመዉሰድ ይተነትናል፣ ማሻሻያ ካሌለዉም መረጃዉን አደራጅቶ ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀርባል፣
  • በኦዲት ግኝቶች ላይ በትክክል የማስተካከያ እርምጃ ስለመወሰዱ ይከታተላል፣
  • ለኦዲት ግኝቶች በወቅቱ ምላሽ መሰጠቱን ይከታተላል፣
  • በሳጥን ዉስጥ ተገኝቶ ቆጠራ በተደረገ ገንዘብና በሂሳብ ማመዛዘኛ ላይ የሚታያዉ ሚዛን ልዩነት ያለባቸዉን የክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች፣ ተቋማት እን አስተዳደር እርከኖችን ለይቶ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
  • የበጀትና ወጪ መግለጫዎችን በማዘጋጃት በክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች፣ በክልል ተቋማት እና በአስተዳደር እርከኖች አለአግባብ የሚወጡ ወጪዎችን በመለየት መረጃዉን ለሚመለከታቸዉ አካላት በማቅረብ ዉሳኔ እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡
  1. የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት
  • መንግሥት ከልማት አጋሮች ጋር የገባዉን የስምምነት የዉል ሰነድና የመሥሪያ ቤቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ መነሻ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ ዕቅድ ማቀድና በዕቅዱ መሠረት ያከናወናል፣
  • በዳይሬክቶሬቱ ሥር ያሉ ቡድኖች የዳይሬክቶሬቱን አመታዊ ዕቅድ መነሻ በማድረግ የእያንዳንዱ ፕሮግራም ሥራዎችን በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ለመፈፀም የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት እቅዶቹ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
  • በዕቅዱ መሠረት ተግባራት የሚከናወንበት ሀብት ከተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶችን መንግሥታት እንዲሁም የመንግሥትና የህብረተሰብ መዋጮች በወቅቱ ተስብስበዉ በሥራ ላይ እንዲዉል ያደርጋል፣
  • የዳይሬክቶሬቱ ሥራ በዕቅዱ መሠረት ዉጤታማ በሆነ መንገድ እንዲፈፀም የሚያስፈልገዉ የሰዉ ኃይልና የተለያዩ ቁሳቁሶች ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ እንዲሟላ ያደርጋል፣
  • ወደ ፕሮግራሞቹ አዲስ ለሚቀለቀሉ ባለሙያዎች በቂ የሆነ ኦሪንቴሽን በመስጠት በተመደቡበት ሙያ ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠናና ግንዛቤ እንዲያገኙ ያደርጋል፣
  • ዕቅዶቹ በወቅቱ እንዳይፈፀሙ የሚያደርጉ ክፍተቶችን መለየት የሚያስችል አሰራር ሥርዓት ይዘረጋል፣
  • እያንዳንዱ ፕሮግራም የተፈቀደዉን በጀት በተግባራትና በኮምፖንት መዝግቦ በመያዝ የጥሬ ገንዘብ ዝዉዉር ሲፈፀም በማቀናንስ ሚዛኑን ወቅታዊ ያደርጋል፣
  • ከተፈቀደዉ በጀት ዉጭ ክፍያ ተፈፅሞ ቢገኝ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፣
  • ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ የእያንዳንዱ ፕሮግራም ሀበት የሚተዳደርበት ስያሜያቸዉ A የሆኑ የባንክ አካዉንቶች እንዲከፈቱ ያደርጋል፣
  • በስምምነቱ ሰነድ መሠረት የፕሮግራሞቹ ተግባራት ማስፈፀሚያ ገንዘብ በወቅቱ ወደ ፕሮግራሞቹ ባንክ አካዉንት ገቢ እንዲሆን አስፈልጊዉን መረጃዎች ለሚመለከታቸዉ አካላት ያቀርባል፣
  • ወደ ፕሮግራሞቹ ባንክ አካዉንት ገንዘብ ገቢ ስለመሆኑ በክልል ደረጃ ፕሮግራሞችን ለሚያስተበብሩ ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች በደብደቤ ያሰዉቃል፣
  • በክልል ደረጃ ፕሮግራሞችን የሚያስተበብሩ ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች ለፕሮግራሞቹ ተጠቃሚ ክልል ቢሮዎች፣ ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎች፣ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የጥሬ ገንዘብ ዝዉዉር ለመፈፀም የጥሬ ገንዘብ ፍላጎት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ እንዲላክ ያደርጋል፣
  • በተላከዉ የጥሬ ገንዘብ ፋለጎት መርሃ ግብር መሠረት ከእያንዳንዱ ፕሮግራም ባንክ አካዉንት የጥሬ ገንዘብ ዝዉዉር ለመፈፀም የሚያስችሉ የበንክ ማዛዣ ደብደቤዎችን በማዘጋጀትና በሚመለከታቸዉ ኃላፊዎች እንዲፈራሙ በማስደረግ ገንዘብ እንዲተላለፍ ያደርጋል
  • በፕሮግራሞቹ ባንክ አካዉንት ዉስጥ ከነበረዉ ገንዘብ ዉስጥ የተከፈለዉን፣ ገቢ የተደረገዉን እን የቀረዉን ሚዛን ለይቶ ለማወቅ የባንክ ዴቢትና ክሬዲት አዲቫይሶችን ይሰበስባል፣
  • የተላለፈዉ ገንዘብ ለተጠቃሚ መሥሪያ ቤቶች፣ ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎች፣ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች በትክክል መድረሱንና በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ሥራ ላይ እንዲዉል ይከታተላል፣
  • የፕሮግራሞቹ ሀብት የሚመራባቸዉ የፕሮግራሞቹን አፈፃፀም መመሪያዎች፣ የስምምነት ሰነዶች የፕሮግራሞቹ አፈጻጸም ዉጤት መላክያ የዉጤት አመልካቾች የሚያሳዩ ሰነዶችን ኮፒ በማድረግ ለፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች ይልካል፣
  • የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች በተላለፉት በህግ ማዕቀፎች መሠረት ተግባሮቻቸዉን መፈፀማቸዉን ይከታተላል፤
  • ከአሰራር ዉጭ የሚተገበሩ ተግባሮችን በመለየት የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግና ለሚመለከታቸዉ አካላት ሪፖርት ያቀርባል፣
  • ድጋፍና ክትትል የሚያስፈልጋቸዉ የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎችን ይለያል፣
  • የፕሮግራሞቹ ሀብት አስተዳደር በሚመራባቸዉ በህግ ማዕቀፎች መሠረት መፈፀሙን ለመከታተል በእያንዳንዱ ፕሮግራም ቼክ ሊስት በማዘጋጀት የድጋፍና የክትትል ሥራዎችን ያከናዉናል፣
  • በድጋፍና ክትትል ዉቅት በተገኙት የአፈፃፀም ክፍተቶች ዙሪያ ከፕሮግራሙ ተጠቃሚ ክልል ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች፣ ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎች፣ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደር አመራር አካላት በተገኙበት ዉይይት በማድረግ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
  • ከድጋፍና ክትትል መልስ ግብረ መልስ በጽሑፍ በመስጠት አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
  • በደጋፍና ክትትል ወቅቱ የተገኙ የአፈጻጸም ክፍተቶችን መነሻ በማድረግ የዉይይት ሰነዶችን በማዘጋጀት የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የወይይት መድረክ በማዘጋጀት ዉይይት በማካሄድ አቅጠጫዎች እንዲቀመጡ በማድረግ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
  • የቻናል አንድ ፕሮግራሞች የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር የሕግ ማዕቀፎችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ስለሚያደርጉ በነዚህና በፕሮግራሞቹ አሰራር መመሪያዎች ላይ የአቅም ግንባታና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በማዘጋጀት ሥልጠና ይሰጣል፣
  • የዉይይት መድረክና የተሰጡ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ፈይዳ በደሰሳ ጥናት በመለየት ክፍተቶችን ያርማል፣
  • ፕሮግራሞችን በተመለከተ በክልል ደረጃ በዓመት ከአራት ጊዜ በላይ የዉይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ፕሮግራሞችን የማስተወቅ ሥራ ያከናወናል፣
  • በእያንዳንዱፕሮግራም አዳዲስ አሰራር ሥርዓቶች ላይ ግንዛቤ ይፈጥራል፣
  • ለእያንዳንዱ ፕሮግራም ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ የሂሳብ መረጃ የሚተዳደርበት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተጋዘ የተቀናጀ የበጀትና የወጪ ሶፍት ዌሪ(IBEX) እንዲዘረጋ በማድረግ መሠረታዊ የሂሳብ ሰነዶችን በመጠቀም በየዕለቱ ምዝገባ ያካሄዳል፣
  • በምዝገባ ሂደት የተፈጠሩትን የጥራት ችግሮችን በመለየት የማስተካከያ ሥራዎች ማድረግ
  • የተስብሳቢና የተከፋይ ሂሳቦች በዕድሜ ዘመናቸዉ በመለያት ሚዛናቸዉን በመቀነስ መረጃዉን አደራጅቶ የመያዝ ሥራ ያከናወናል፣
  • እያንዳንዱ ፕሮግራም በመንግሥትና በልማት አጋሮች ሪፖርት ፎርማት መሠረት ከፕሮግራሙ ተጠቃሚ ክልል ቢሮዎችና ተቋማት፣ ኮሌጆች፣ ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎች፣ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች በየወሩ፣ በሩብ ዓመት፣ በግማሽ ዓመት አመታዊ የፋይናንሻልና የፊዚካል ሪፖርቶችን በተሟላ ሁኔታ ጥራቱን የጠበቀ መሆኑን በማረጋገጥ ይሰበስባል፣
  • የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ክልል ቢሮዎችና ተቋማት፣ የዞኖች፣ የልዩ ወረዳዎች፣ የወረዳዎች እና የከተማ አስተዳደሮች ሪፖርቶችን በክልል ደረጃ በእያንዳንዱ ፕሮግራም ስም ዝርዝር ሪፖርቶች በማዘጋጀት በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ለልማት አጋሮች፣ ለፌዴራል መንግሥት እና ለሌሎች ለሚመለከታቸዉ አካላት ተደራሽ ያደርጋል፣
  • የተላኩ የፋይናንሻያልና የፊዝካል ሪፖርቶችን መነሻ በማድረግ የሚሰጡ ግብረ መልሶችን ተቀብሎ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፣
  • ከፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች የቀረቡ ረፖርቶችን መነሻ በማድረግ ግብረ መልስ ይሰጣል፣
  • በመንግሥትና በልማት አጋሮች መካከል በተደረገዉ የስምምነት ሰነድ መሠረት እያንዳንዱ ፕሮግራም ከአገር ዉስጥ ከአገር ዉጭ በሚመጡ በልማት አጋሮችና በመንግሥት አካላት በቅንጅትና በተናጣል በፕሮግራሙ በተፈቀደዉ ሀብት መሠረት የተከናወኑ ተግባራት በዕቅዱ መሠረት ምን ያህል ከዉጤት፣ ከወጪ፣ ከጊዜ እና ከጥራት አንፃር በተመረጡ ወረዳዎችና ዞኖች በአካል በመገኘት ግምገማ በማድረግ ግብረ መልስ የሚሰጥበትን ሁኔታ ይፈጥራል፣
  • የግምገማዉን ዉጤት መነሻ በማድረግ በክልል ደረጃ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ባለድርሻ አካላት በሚገኙበት ዉይይት የሚደረግበት መድረክ ያዘጋጃል፣
  • በእያንዳንዱ ፕሮግራም በክልሉ ስለተከናወኑ ተግባራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በማቅረብ ዉይይት እንዲደረግበት ያደርጋል፣
  • ፕሮግራሞችን በሚመለከት በፌዴራልና በልማት አጋሮቻችን አማከይነት በሚዘጋጀዉ መድረክ ላይ በመገኘት ስለ ክልሉ ፕሮግራሞች ሪፖርት ያቀርባል፣
  • እያንዳንዱን ፕሮግራም በሚመለከት በኤልክትሮኒክስ የመረጃ አላለክ ዘዴ በየዕለቱ የሚፈለጉ መረጃዎችን ለመረጃ ፈላጊዎች ይሰጣል፣
  • በአካል ተገኝቶ መረጃ ለሚወስዱ ከአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ ለሚመጡ ለልማት አጋሮችና ለሌሎችም አካላት የተቀናጀ መረጃ ይሰጣል፣
  • የእያንዳንዱን ፕሮግራም የሀብት አጠቃቀም የሂሳብ ሰነዶች በአግባቡና በቀላሉ መገኘት በሚያስችል ሁኔታ በሰነድ ክፍል ተደራጅቶ እንዲቀመጥ ያደርጋል፣
  • የእያንዳንዱ ፕሮግራም የሀብት አስተዳደር እንቅስቃሴ በፕሮግራሙ ተጠቃሚ ክልል ቢሮዎች፣ ተቋማት፣ ኮሌጆች፣ ዞኖች፣ ልዩ ወረዳ፣ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር የዉስጥ ኦዲተሮች ኦዲት እንዲደረግ ያደርጋል፣
  • በመንግሥትና በልማት አጋሮቻችን መካከል በተደረገዉ የስምምነት ሰነድ መሠረት በተመረጡ በዉጭ ኦዲተሮች የእያንዳንዱ ፕሮግራም ሀብት አስተዳደርና አጠቃቀም ሂደት ኦዲት እንዲደረግ ያደርጋል፣
  • በኦዲት ሥራ ወቅት በተገኙት ኦዲት ግኝቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ ግብረ መልሱን ኦዲት ለተደረጉት አካላት በወቅቱ በመላክ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
  • የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች በተገኙት ኦዲት ግኝቶች ላይ በትክክል የማስተካከያ እርምጃ ስለመዉሰዳቸዉ ኦዲት በተደረጉት መሥሪያ ቤቶች በአካል በመገኘት አፈጻጸሙን ይፈትሻል፣
  • በኦዲት ግኝቶች ላይ በወቅቱ የማስተካከያ እርምጃ ተወስደዉ ለሚመለከታቸዉ አካላት የተሟላ ማስረጃ የማይቀርብ ካሆነ የፌዴራል መንግሥት ለክልላችን ከሚያስተላለፈዉ የድጎማ ገንዘብ ቀንሶ የሚያስቀር በመሆኑ የኦዲት ግኝቶችን መነሻ በማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት ለማካሄድ መድረክ ያዘጋጃል፣
የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት በሶስት ቡድኖች የሚከፋፈል ሲሆን ተግባራቸዉም ከዚህ በታች በተመለከተዉ ሆኑታ ይሆናል፡፡
  1. የኢኮኖሚ ዘርፍ ቻናል አንድ ፕሮግራሞች ሀብት አስተዳደር ቡድን
በኢኮኖሚ ዘርፍ በሚገኙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች  ዉስጥ የሚተገበሩ የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ፈንድ በፕሮግራሞቹና በመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር አፈጻጸም መመሪያዎች መሠረት የሚመራበትን አሰራር ሥርዓት ተከትሎ  ወቅታዊ፣ ጥራቱን የጠበቀ እና የተሟላ የፋይናሻልና የሂሳብ ሪፖርቶችና መረጃዎች እየቀረቡ ለሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ተደራሽ የሚደረግበትን ተግባራት ያከናዉናል፡፡
  1. የማህበራዊ ዘርፍ ቻናል አንድ ፕሮግራሞች ሀበት አስተዳደር ቡድን
በማህበራዊ ዘርፍ በሚገኙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች  ዉስጥ የሚተገበሩ የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ፈንድ በፕሮግራሞቹና በመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር አፈጻጸም መመሪያዎች መሠረት የሚመራበትን አሰራር ሥርዓት ተከትሎ  ወቅታዊ፣ ጥራቱን የጠበቀ እና የተሟላ የፋይናሻልና የሂሳብ ሪፖርቶችና መረጃዎች እየቀረቡ ለሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ተደራሽ የሚደረግበትን ተግባራት ያከናዉናል፡፡
  1. የአገልግሎት ዘርፍ ቻናል አንድ ፕሮግራሞች ሀብት አስተዳደር ቡድን
በአገልግሎት ዘርፍ በሚገኙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች  ዉስጥ የሚተገበሩ የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ፈንድ በፕሮግራሞቹና በመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር አፈጻጸም መመሪያዎች መሠረት የሚመራበትን አሰራር ሥርዓት ተከትሎ  ወቅታዊ፣ ጥራቱን የጠበቀ እና የተሟላ የፋይናሻልና የሂሳብ ሪፖርቶችና መረጃዎች እየቀረቡ ለሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ተደራሽ የሚደረግበትን ተግባራት ያከናዉናል፡፡
  1. የኢንፎርሜሽን ኮሙኒክሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት
  • የዳይሬክቶሬቱን ሥራ በማቀድ፣ በመምራት፣ በማስተባበር፣ አፈጻጸሙን በመከታተልና በመገምገም ውጤታማ ማድረግ፣የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ሥራዎችን መከታተል፡የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የአሰራር ስርዓቶች  በአግባቡ መዘርጋታቸዉን ለማረጋገጥ ነው
  • የሀገሪቱን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስትራቴጂ መሰረት በማድረግ ከመስሪያ ቤቱ ተልእኮ ጋር የሚጣጣም የመ/ቤቱን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስትራቴጂናመሪ ዕቅድ መዘጋጀቱን ይከታተላል፣በየጊዜውም እንዳስፈላጊነቱ ማሻሻያ ያደርጋል፡፡
  • ከዘርፉ ስትራቴጂክ ዕቅድ የተመነዘረ የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣
  • የዳይሬክቶሬቱን ዝርዝር ተግባራትን ያቅዳል፣ ያደረጃል፣ ይመራል፣ይወስናል ፣አፈጻጸሙንይቆጣጠራል ይከታተላል፣ ይገመግማል።
  • በሰሩ የሚገኙ የቡድን መሪዎችንይደግፋል፣ይቆጣጠራል ይከታተላል፣ ይገመግማልበየወቅቱ ይመዝናል፤ በምዘናው ውጤት መሠረትም ቀጣይ ተግባራትን ያካናውናል፣
  • በተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች በሚሰጠው የሥልጣን ውክልና መሠረት በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽንቴክኖሎጂ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ወይም የሚሰጡ ውሳኔዎችን ተግባራዊነት ይከታተላል፣
  • በመ/ቤቱ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ በመታገዝ ማሻሻያና ማስፋፊያ የሚፈልጉ አዳዲስ ፍላጎቶች ሲኖሩ የጥናት ቡድኖች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል ይከታተላል፣
  • የመስሪያ ቤቱን አሰራር በኮምፒውተር የታገዘ ለማድረግ በተጠናና በተቀናጀ መንገድ ደረጀ በደረጃ ተግባራዊ የሚያደርግ የመስሪያ ቤቱን ቁልፍ ተግባራት በሶፍትዌር የታገዙ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
  • የመስሪያ ቤቱን ድረ-ገፅ በማደራጀት አዳዲስ አሠራሮችን በየጊዜው በማካተት ትክክለኛና ወቅታዊ የመረጃ ፍሰት ለተጠቃሚዎች እየደረሰ መሆኑን ማረጋገጥ፡፡
  • በመረጃቋቶች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን በመለየት ለመከላከል ወቅታዊ የሆኑትን የመከላከል ሶፍትዌሮችና የሴኩሪቲ ሲስተሞችን ያደራጃል ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል፡
  • የመሥሪያ ቤቱን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት፣ የመረጃዎች፤ የሃርድዌርና የሶፍትዌር፤ የዳታ ሴንተር እና አጠቃላይ የአይሲቲ ሃብቶች ደህንነት የሚጠበቅበትን መንገድ ፖሊሲ ይቀርፃል፤ ያዘጋጃል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡
  • የሶፍትዌር ላይሰንስና የመረጃዎች ቅጅ በአግባቡ መያዙን ክትትል ያደርጋል፡፡
  • የአይሲቲ ኘሮጀክቶችን ያቅዳል መፍትሄ አቅራቢ ድርጅቶችን ለመጋበዝና ለመምረጥ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ለማዘጋጀት በሚደረገው ሂደት አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፡፡
  • የሴተክተሩን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ያሰተባብራል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፤
  • በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሴሚናሮችና በመሳሰሉት ስብሰባዎች ላይ መ/ቤቱን በመወከል ይሳተፋል፡፡
  • የዳይሬክቶሬቱ ሠራተኞች በተቀመጡ እሴቶች መሠረት በስነምግባር እና በባለቤትነት ስሜት እንዲሰሩ እና ቀልጣፋ እና ውጤታማ እንዲሆኑ የኮቺንግ (Coaching) ሥራ ያከናውናል፣ አስፈላጊ የሥራ ግብዐቶች እንዲሟሉላቸው ያደርጋል፣
  • የዳይሬክቶሬቱን ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም ለበላይ አካል ሪፖርት ያቀርባል፣
  • የመሥሪያ ቤቱን የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ፍላጎት ጥናትን በበላይነት ይመራል
  • አዳዲስና ነባር የኔትወርክ ሲስተሞች የጥራት ደረጃ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችሉ መንገዶችን ይቀይሳል፤
  • የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ሲፈቀዱጥራታቸውን ጠብቀው በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ መተግበራቸውን  ክትትል ያደርጋል፣
  • የመ/ቤቱን የኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
  • የመ/ቤቱን የኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣
  • የመ/ቤቱ የመረጃ ፍሰት ዓይነትና መጠን የመለየት ጥናት ሲካሄድ በከፍተኛ ሃላፊነት በበላይነት ይከታተላል ፤
  • ለመ/ቤቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት የሚውሉ የሶፍትዌርና ሃርድዌር መሣሪያዎች ስፔስፊኬሽን ትክክለኛነት ያረጋግጣል፣ በትክክል መስራታቸዉንና አገልግሎት ላይ መዋላቸውን በበላይነት ይቆጣጠራል፣
  • ደረጃዉን የጠበቀ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፖሊሲ እንዲዘጋጅ በበላይነት ያስተባብራል፤ ክትትል ያደርጋል፤
  • የመ/ቤቱን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣
  • የመ/ቤቱ የኢንፎርሜሽን ኮሙኑኬሽን ፖሊሲ ዶክምንቶች በአግባቡ መሰራታቸውን ይከታተላል፣
  • የመስሪያ ቤቱ ሠራተኞች የዲጅታል ቶክ ሎጂ (e-mail, Internet, etc.) ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለሠራተኞች የሚመጥን መሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ሥልጠና መዘጋጀቱን ሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፡፡
  • በየቡድኖቹ የሚዘጋጁ የአጠቀቀምና የስልጠና ማንዋሎች ይገመግማል፣ ማስተካከያ በማድረግ የመጨረሻ ቅርፃቸውን እንዲይዙ ያደርጋል ፣
  • የመ/ቤቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት አሰጣጥ በተጠቃሚዎች እንዲገመገም ያደርጋል ፤
  • ከተጠቃሚዎች የሚነሱ የአሰራር ችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
  • ኮምፒውተራይዝ ተደርገው ሥራ ላይ የዋሉ ሲስተሞችን በየጊዜው አፈፃፀማቸውን በመገምገም አስፈላጊውን ማሻሻያ እንዲደረግላቸው ክትትል ማድረግ፣
  • ለIFMIS ትግበራና ለሌሎች አዳድስ የአሰራር ሥርዓት ለሚዘረጋው ቅድሜ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ ያዘጋጃል፤
  • ስለ ተከናወኑ ተግባራት ሰለአጋጠሙ ችግሮች እንዲሁም ስለተወሰዱ እርምጃዎች ወቅቱን የጠበቀ ሪፖርት ያቀርባል፣
  • የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ፣ የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ዓመት ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ለቅርብ ኃላፊና ለቢሮ በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ያቀርባል፣
  • ዳይሬክቶሬቱን በሚመለከቱ በተለያዩ ስብሰባዎች፣ሴሚናሮች ላይ በመገኘት የልምድ ልዉዉጦችንና ግንዛቤ በመቀመር በዳይሬክቶሬት ሥር የሚገኙ ባለሙያዎችን ዉጤታማ የሆነ ሥራ እንዲያከናወኑ ማድረግ፣የተገልጋዮችን እርካታ ደሰሳ ጥናት እንዲካሄድ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የሚሻሻልበት ሁኔታ ይቀይሳል፣
  • በዳይሬክቶሬቱ የሰዉ ኃይል በመዋቅሩ መሠረት እንዲሟላ ያደርጋል፣
የፊስካል ፖሊስ፣የሲቪክና ትብብር ዘርፍ
የአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ
የኢንስፔክሽንና ውስጥ ኦዲት ዘርፍ
የክፍያና ሂሳብ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
በክልልና በታችኛው እርከን ስለሚኖር አደረጃጀት

የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት

  • መንግሥት ከልማት አጋሮች ጋር የገባዉን የስምምነት የዉል ሰነድና የመሥሪያ ቤቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ መነሻ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ ዕቅድ ማቀድና በዕቅዱ መሠረት ያከናወናል፣
  • በዳይሬክቶሬቱ ሥር ያሉ ቡድኖች የዳይሬክቶሬቱን አመታዊ ዕቅድ መነሻ በማድረግ የእያንዳንዱ ፕሮግራም ሥራዎችን በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ለመፈፀም የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት እቅዶቹ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣
  • በዕቅዱ መሠረት ተግባራት የሚከናወንበት ሀብት ከተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶችን መንግሥታት እንዲሁም የመንግሥትና የህብረተሰብ መዋጮች በወቅቱ ተስብስበዉ በሥራ ላይ እንዲዉል ያደርጋል፣
1234.jpg

Do you need Sidama National Regional State Finance Bureau? Please Click contact Us

Address

address: Beside of Hawassa City Primary Court

phone (+251) 13181046

Email : snrsbof@snrsfb.gov.et

Fax(046)-220-60-84        

PostP.S.K. 485

Usefull Links

Announcement

Bid

Vacancy

Contact

 

Social Media

FaceBook

Youtube

Google Map

     WhatsApp

     Telegram