በሲዳማ ክልል ከUN OCHA የመጡ አካላት ጋር በHumaniterian Responce ዙሪያ የክልሉ ትምህርት፤ ጤና፤ ግብርና፤ ውሃ ማእድንና ኢነርጂ፤ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮዎች እንዲሁም የጤና ኢንስቲትዩት እና የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የሚመለከታቸው ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት በክልላችን ነባራዊ ሁኔታ እና UN OCHA በአጋርነት ሊደግፍ በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አራርሶ ገረመው (ዶ/ር) በቢሮዋቸዉ ተቀብሎ ውይይት አድርገዋል።
በመድረኩ የተገኙ ቢሮዎች ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎችንና UN OCHA በቀጣይ አብሮ መስራት የሚገባቸውን የልማት ክፍተቶች የሚያስረዱ ጽሁፎች አቅርበው ከድርጅቱ ተወካዮችም ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተሰጥተውበታል።
በመጨረሻም የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊው አጠቃላይ ክልላዊ የስነ ህዝብ ሁኔታዎች እና የልማት ክፍተቶች በክልሉ የአጋር ድርጅቶችን የጋራ የነቃ ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን እና በክልሉ ያለው የሠላምና ፀጥታ እንዲሁም በዕቅድ የሚመራው የመልማትና የማደግ ፍላጎት መልካም ዕድል መሆኑን ገልፀው UN OCHA ወደ ክልላችን በመምጣት በጋራ ለመስራት ያሳየውን ፍላጎት አድንቀውና አመስግነው በቀጣይ በአጭር ጊዜ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች መግባት እንዲቻል አበክረው ገልጸዋል።
የካቲት 26/2016 ዓ.ም የፋይናንስ ቢሮ ህዝብ ግኑኝነት
ሀዋሳ

