የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓትን መተግበር የጊዜና ጉልበት ብክነት ከማስቀረቱ ባሻገር ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን በማስፈን በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን የሚያጎለብት መሆኑንም በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ አስታውቋል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ እና ፔራጎ እንፎርሜሺን ኋ.የተ.የግ.ማ. ከሚባል ሶፋትዌር ድርጅት መካከል የተመረጡ መንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ኢ.ጂ. ፒ. (eGP) ፕሮግራም ተግባራዊ ለማድርግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አራርሶ ገረመው ከጨረታ ሂደት ጋር በተያያዘ የወረቀት ንኪክና የጊዜና የጉልበት እንዲሁም አለአግባብ የሚወጡ የተለያዩ ወጪዎችን ማስቀረት መቻሉን ጠቁመው፤ በከፍተኛ ሁኔታ የመንግስት ሀብት ከብክነት ማዳን መቻሉን በአስተያየታቸው አብራርተው የዛሬው ሥምምነት ለክልላችን ታሪካዊ ሥምምነት መሆኑን ገልፀው ወደዚህ መተግበሪያ ተጠቃሚነት ውስጥ የሚገቡ ቢሮዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለህዝባቸው ባለውለታ ናቸው ብለዋል ።
ኃላፊው አክሎም በሲዳማ ብሔራዊ ክልል ፋይናንስ በሥሩ ያሉ 50 የሚደርሱ ቀጥታ online ሥራ መጀመሩን ጨምረው ገልፀው በቀጣይም የchek አልባ ፋይናንስ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ እንዳሉት ባለስልጣኑ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓትን መተግበር ግልጽነትና ተጠያቂነትን በማስፈንና ብልሹ አሠራርን በማስወገድ በመንግስትና በህዝብ መካከል መተማመን እንዲኖር ያደርጋል" ብለዋል። አክሎም የሲዳማ ክልላዊ መንግስት ይህን መተግበሪያ ተቀብለው ከሁሉም ክልሎች ቀዳሚ በመሆን ተግባራዊ በማድረጋቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ ሀሳባችን ተቀብሎ ወደ ሥራ እንድንገባ ሌተቀን ድጋፍ ማድረጋቸውን አመስግነዋል።
የፋይናንስ ቢሮ ህዝብ ግኑኝነት ዳይረክቶሬት
ቀን ህዳር 3/3/2016 ዓ.ም
ሀዋሳ


