news

Previous Next

ESAP3  -  IDA20  በዓለም አቀፍ ባንክ ሲተገበር ቆይቶ መንግሥት እንድመራው በመደረጉም እንኳን ደስ አለን፡፡ እንደሚታወቀው የሚዳሰስም ሆነ የማይዳስሰው ሃብት፤ ገንዘም ሆነ የሰው ልጅ ክህሎት፣ እውቀት እና ጉልበት፡ የተፈጠረው ለሰው ልጆች ጥቅም እንደውል ነው፡፡ ለህዝብ፡ ጥቅም ሲውሉም በጨለማ፣ በግርዶሽ የሚዉል፡ መሆን፡ የለባቸውም፡፡ ይልቀን አሣታፊ፣ አቃፊ፣ ግልፅ፣ ከአግለይነት የፀዳ፣ ኃላፈነት፡ በተሞላበት መሆን፡ አለባቸው፡፡ ለዚህም፤ ከህዝብና ከመንግሥት፣ የተቀበልነውን አዳራ መወጣትን ይጠይቃል፤ በተጨማሪም ከማናየው ነገር ግን በግላጭ ከሚያየን ፈጣሪ እና አብሮን፡ ከሚኖር ሂሊናችን ሊያጋጨን፡ የሚችል ተግባር መፈፀም አይገባንም፤ ይልቁን በትልቅ ጥንቃቂ፡ የሃብት፡ አስተዳደር ሥርዓታችን፡ ሊጎለብት ይገባል፡፡ ተጠያቂነትንና ጠያቂነትንም ልናበዛ ግድ ይለናል፡፡

በክልላችን ሞጋች፣ አመንኮኖያዊ፣ አግባባዊ፡ ጠያቂ ንቁ፣ የበቃ፣   የሚያበቃ፣ ነገሮችን አርቆ ተመልካች እና አመልካች ሰዎች እንዲፈጠሩ ተግተን፡ መሥራት ጊዜ የምንስጠው ጉዳይ፡ አይሆንም፡፡ እንደምታውቁት፡ ሲዳማ መንግሥት ከሆነበት ማግሥት አንሥቶ መላው፡ የክልላችን ነዋሪዎች በዓመቱ ውስጥ ምን ያክል ሃብት፡ እንደተመደበ የተመደበው ሃብት በዬትኞቹ ኘሮጀክቶች ላይ፡ እንደሚውል፤ ግልፀኝነትን ለመፈጠር እያደርግን ያለው ጥረት እንደ ቢሮአችን፡ የሚደነቅ ተግባር ነው፡፡ በESAP3፡ ኘሮጀክት ድጋፍም በተለይ በ8 ወረዳዎች እየፈፀምን ያለው ተግባር ለሌሎች ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ነው፤ በየቀበሌያቱ የሚገኙ ማህበረሰብ አቀፍ ኮሚቴዎችም የበለጠ እንዲተጉ፡ ማድረግ እንደተጠበቀ ሆኖ፡፡

የተከበራችሁ፡ የዚህ ኘሮግራም ተሣታፍዎች ሁላችሁም እንደምትረዱት የሰው ልጅ ፍላጎትና ያለን፡ ሃብት፡ ልጣጠም አይችልም፤ የአኮኖሚ ደረጃ፤ የአኗኗር ዜደአችንም የተለያየ ነው፡፡ ስለዚህ፡ አድሎኦዊነት፡ ቀርቶ፡ የምናገኛትን፡ ሃብት፡ ዜጎች በግልፅ እንዲያውቁ፤ የልማት፡ ሴክተር ኘሮጀክቶችም ዬት? መቼ? እና እንዴት፡ እንደሚፈፀሙ በጋሃድ ማሣወቅ ከራሥ ባለፈ፡ ለትውልድ ማሰብ፡ ይጠበቅብናል፡፡

በተጨማሪም የእጅ ንፅህናችንን በማጎልበት፣ ነገሮች ከመበላሸታቸው አስቀድሞ በመጠንቀቅ፤ የጠባቂነት እና ዓይን አፋርነት ቀርቶ፡ ሁሉም ዜጋ በንቃት ስለሚመደብለት ሃብት በምክናታዊነት ሽንጡን ገትሮ የሚሟገት እንዲሆን እንድናበቃው የአደራ መልዕክቴ ነው፡፡ ከአካል ጉዳተኞች፣ በህመም ምክንያትም የሚገለሉ፣ የሚዘነጉ፣ እና የሚሸማቀቁ በክልላችን እንዳይኖሩ፡ የዕይታ አድማሳችን የእናት፡ አይን እንዲሆን፡ ጥሪዬ ነው፡፡ ተጠቃሚ ዜጎቻችንም፡ ሆይ!! ለእናንተ አገልግሎት ይሰጥ ዘንድ በመንግሥታችሁ፡ የተሠሩ ቀን፡ ሲበሩ፡ ማብራት ብታዩ እንዲጠፉ መንገር፣ የተበላሹ የውሃ ተቋማትን ባያችሁ፡ ጊዜ ተባብሮ ማስተካኪል አሊያም ቢግልፅ፡ ለወረዳው አመራር እንድትጠቁሙ በየመንገዱ፡ ቆሻሻ እንዳይጣል፡ መጠንቀቅ እና ኘሮጀክቶች ከመጀመራቸው አስቀድሞ በሚደረግ፡ የተፈላጊነት ጥናቶች በቂ፡ እውቀት እንዲኖራችሁ፡ እንድትተጉ፡ አሳስባለሁ፡፡

የዚህ ኘሮግራም አስተባባሪዎች ዛሬ በ8 ወረዳዎች ባደረጋችሁት ድጋፍ፡ ለሌሎች ወረዳዎችም ትምህረት የሚሆን፡ ውጤት እያየን፡ ነው፡፡ እንደ መንግሥት matching fund እንኳን ይዘን ለማስፋፋት ልባችሁንና አእምሮአችሁን በማዋሃድ ከዚህ ወደ ቢሮአችሁ፡ ስትመለሱ፡ ቀና ምላሽ፡ እንድትሰጡና ክልላችን በዚህም ዜጎችን ሞጋች እና ብቁ ለማድረግ፡ የያዝነውን አቂም እንድምትደግፍ ጽኑእ እምነት አለኝ፡፡

የየወረዳ፡ እና የከተማ አስተዳደሪዎች ተጠቃሚዎች ከሚያዩት በላይ ህሊናና ፊጣሪ፡ ዘወትር ያየናልና በቅንነት፡ ለማገልገል፡ ከተጋነው በላይ፡ እንድትተጉ፡ ላበረታታችሁ፡ እወዳለሁ፡፡ በመጨረሻም ይህንን፡ ኘሮግራም በክልላችን እንድተገበር ለመሥራት የተመረጣችሁ PLCDዎች፡ ከሥራ ፈጠራ ማስፋፋት አኳያ፤ ለሥራው ቅልጥፍና፤ የተቋማችሁ፡ ደንብ፡ በሚያዘው መሠረት የአካባቢ ወጣቶችን ለቦጎ ፍቃዲኛ ወጣቶቻችን የሥራ ዕድል እንደምትፈጥሩ እምነቱ፡ ቢኖረኝም፡ በዚህ አጋጣሚ ለበረታታችሁ እፈልጋለሁ፡፡ በምክንያታዊነት የሚያምን ዜጋ መፈጠር አቋማችን፡ ነው!

Previous Next

የሲዳማ ህዝብ፡ ከ100 ዓመታት የፓለቲካ ትግል በኃላ፣ የቀደመ የመንግሥት፡ አስተዳደሩን በመመለስ እነሆ በዚህ በለውጥ ዘመን የለውጥ ዕይታ ይዞ፡ ሀገራችንንም፡ በተገባላት፡ ቃል ኪዳን መሠረት ፡ ዐለቷ እንዲ ፀና እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ዋጋው፡ ከፍ ያለ ነው፡፡ የኢትዮጱያ ድምቀት በመሆናችን እንኳን ደስ አለን!!

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፡ በህብረ- ብሔራዊነት የሚያምን፣ በኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት የማይደራደር  ኢኮኖሚዉም ጎልብት፡ የፋይናንስ ስርዓቱንም ዘምነው የአፍርካ የኩራት ኮከብ፡ እንድትሆን የሚተጋ፤ ክልላችን አምርቶ  ለዓለም ገበያ ከሚያቀርበው አሬንጋዴ ወርቅ ቡና፡ አንሥቶ፡ ሌሎች ምርቶችንም በማምረት ላይ የሚገኝ፡ ሰው ገናና ልማቶች ብልጽግና እውን፡ የሚሆነውም፡ የኢኮኖሚ መረጋጋት አይነተኛ አጀንዳ፡ የሆኑዉን ስንረዳ ነው፡፡ በምድራችን ያለው፡ ሃብት ውስን ሆኖ ፍላጎት ቢለያይም፣ አጣጥም መምራት ደግም ከእኛ  ይጠበቃል፡፡ ውስን፡ ሃብትን አጣጥም፡ ለመምራት፣ የፋይናንስ ስርዓትን፣ ቀልጣፉ፣ወጪ ቆጣቢ፣ ተዓማኒ፣ ግልፅ፣ የቁጥጥር ስርዓቱ የጎለበተ፣ የበጀት ኢያያዝና አጠቃቀም፡ የዘመነ ለማድረግ፡ በዘርፉ ለተሰማሩ፡- እውቀትን፣ ክክሎትን፣ ልምድን፣ ጥበብንና እውነትን፡ ማስተማር እንደሚስፈልግ ባለፈው ዓመት ባዳረግነው ምዘና ለመረዳት ችለናል፡፡

በመሆኑም ቢሮአችን ከፌደራል ገንዘብ ሚ/ር ከIPF  ኘሮጀክት ባገኘው የጋዘብ ድጋፍ እነሆ፡ በ2 ዙሮች 750 ባለሙያ፡ ዘማቶችን  ከወረዳ እስከ ክልል ባሉ መሠሪያ ቤቶች የፋይናንስ ዘርፍ ባለሙያዎችን ለማሰልጠን ችለናል፡፡ ስልጣኞች ከዚህ በኃላ ተግባራችሁን፡ በፉይናንስ ህግና ደንብ  መሠረት የምትሠሩ፣ በአስቻጋር፡ ምክንያቶች የማትሽነፍ፡ ሃቅንና ቅንነትን፣ ቅልጥፈናንና ብልህነትን በማዳበር የያለፈውን ዘመን በአመርቂ ሥራ እንዲትበቀሉ እያሳስብሁ፡ ለዚህ ስልጠና ስከት የደከማችሁትን በሙሉ አመሰግናለሁ፡፡

Previous Next

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለክለል ቢሮዎች፣ ለወረደዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለፋይናንስ ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች በበጀት አስተዳደር፣ በሂሳብና ሪፖርት፣በመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት፣ በኦድትና ቁጥጥር እንድሁም የግዥና ንብረት አስተዳደር ዙርያ ከፈደራል ገንዘብ ሚኒስተር በተገኘዉ በIPF በጀት ድጋፍ በሁለት ዙር ለ7 ተከታታይ ቀናት ስሰጥ የነበረ ስልጠና፡፡


About Us

የሲዳማ ህዝብ፡ ከ100 ዓመታት የፓሌቲካ ትግል በኃላ፣ የቀደመ የመንግሥት፡ አስተዳደሩን በመመለስ እነሆ በዚህ በለውጥ ዘመን የለውጥ ዕይታ ይዞ፡ ሀገራችንንም፡ በተገባላት፡ ቃል ኪዳን መሠረት ፡ ዐለቷ እንዲ ፀና እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ዋጋው፡ ከፍ ያለ ነው፡፡ የኢትዮጱያ ድምቀት በመሆናችን እንኳን ደስ አለን!!

Flickr Photos

Address

address: Beside of Hawassa City Primary Court

phone (+251) 13181046

Email : snrsbof@snrsfb.gov.et

Fax(046)-220-60-84        

PostP.S.K. 485

Usefull Links

Announcement

Bid

Vacancy

Contact

 

Social Media

FaceBook

Youtube

Google Map

     WhatsApp

     Telegram