news

Previous Next

በሲዳማ ክልል ከUN OCHA የመጡ አካላት ጋር በHumaniterian Responce ዙሪያ የክልሉ ትምህርት፤ ጤና፤ ግብርና፤ ውሃ ማእድንና ኢነርጂ፤ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮዎች እንዲሁም የጤና ኢንስቲትዩት እና የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የሚመለከታቸው ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት በክልላችን ነባራዊ ሁኔታ እና UN OCHA በአጋርነት ሊደግፍ በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አራርሶ ገረመው (ዶ/ር) በቢሮዋቸዉ ተቀብሎ ውይይት አድርገዋል።

በመድረኩ የተገኙ ቢሮዎች ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎችንና UN OCHA በቀጣይ አብሮ መስራት የሚገባቸውን የልማት ክፍተቶች የሚያስረዱ ጽሁፎች አቅርበው ከድርጅቱ ተወካዮችም ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተሰጥተውበታል።

በመጨረሻም የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊው አጠቃላይ ክልላዊ የስነ ህዝብ ሁኔታዎች እና የልማት ክፍተቶች በክልሉ የአጋር ድርጅቶችን የጋራ የነቃ ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን እና በክልሉ ያለው የሠላምና ፀጥታ እንዲሁም በዕቅድ የሚመራው የመልማትና የማደግ ፍላጎት መልካም ዕድል መሆኑን ገልፀው UN OCHA ወደ ክልላችን በመምጣት በጋራ ለመስራት ያሳየውን ፍላጎት አድንቀውና አመስግነው በቀጣይ በአጭር ጊዜ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች መግባት እንዲቻል አበክረው ገልጸዋል።

የካቲት 26/2016 ዓ.ም የፋይናንስ ቢሮ ህዝብ ግኑኝነት

ሀዋሳ

Previous Next

 

የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓትን መተግበር የጊዜና ጉልበት ብክነት ከማስቀረቱ ባሻገር ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን በማስፈን በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን የሚያጎለብት መሆኑንም በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ አስታውቋል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ እና ፔራጎ እንፎርሜሺን ኋ.የተ.የግ.ማ. ከሚባል ሶፋትዌር ድርጅት መካከል የተመረጡ መንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ኢ.ጂ. ፒ. (eGP) ፕሮግራም ተግባራዊ ለማድርግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አራርሶ ገረመው ከጨረታ ሂደት ጋር በተያያዘ የወረቀት ንኪክና የጊዜና የጉልበት እንዲሁም አለአግባብ የሚወጡ የተለያዩ ወጪዎችን ማስቀረት መቻሉን ጠቁመው፤ በከፍተኛ ሁኔታ የመንግስት ሀብት ከብክነት ማዳን መቻሉን በአስተያየታቸው አብራርተው የዛሬው ሥምምነት ለክልላችን ታሪካዊ ሥምምነት መሆኑን ገልፀው ወደዚህ መተግበሪያ ተጠቃሚነት ውስጥ የሚገቡ ቢሮዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለህዝባቸው ባለውለታ ናቸው ብለዋል ።
ኃላፊው አክሎም በሲዳማ ብሔራዊ ክልል ፋይናንስ በሥሩ ያሉ 50 የሚደርሱ ቀጥታ online ሥራ መጀመሩን ጨምረው ገልፀው በቀጣይም የchek አልባ ፋይናንስ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀጂ ኢብሳ እንዳሉት ባለስልጣኑ የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ስርዓትን መተግበር ግልጽነትና ተጠያቂነትን በማስፈንና ብልሹ አሠራርን በማስወገድ በመንግስትና በህዝብ መካከል መተማመን እንዲኖር ያደርጋል" ብለዋል። አክሎም የሲዳማ ክልላዊ መንግስት ይህን መተግበሪያ ተቀብለው ከሁሉም ክልሎች ቀዳሚ በመሆን ተግባራዊ በማድረጋቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ ሀሳባችን ተቀብሎ ወደ ሥራ እንድንገባ ሌተቀን ድጋፍ ማድረጋቸውን አመስግነዋል።
የፋይናንስ ቢሮ ህዝብ ግኑኝነት ዳይረክቶሬት
ቀን ህዳር 3/3/2016 ዓ.ም
ሀዋሳ
Previous Next
 
 
ለሀብት ማግኛ መንገዱ የፋይናንስ ስርዓቱ ተአማኒነት ማድረግ እና ስርዓት የሚመራው ማድረግ እንደሆነ የሲዳማ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አራርሶ ገረመው ገለጹ።
በሀገራችን የልማት አጋር የሆኑት የUK መንግሥት ተወካዮች በቀጣይ ድጋፍ ለማድረግ በክልሉ ያለውን አሠራር ለመገምገም ዛሬ ወደ ክልሉ ፋይናንስ ቢሮ መምጣታቸውን ተገልጿል ።
በቢሮ ገለፃም ተደርጎላቸው። በቢሮ ካገኙት መነሻ ወደ መረጡአቸው ወረዳዎችና ክልል ቢሮዎችም በመሄድ ያለውን ሁኔታ ይቃኛሉ ተብለዋል።
እዚህ የሚወስዱት መረጃ ባጠቃላይ ጠቀሜታው እንደ ሀገር ከመመዘኑ ባለፈ ለassessment ከተመረጡ 4 ክልሎች መካከል ሲዳማ አንዱ መሆኑ የበለጠ በፋይናንስ ስርዓት ዙርያ የበለጠ እንድንተጋ ከማገዙም ባለፈ ለልምድ የሚመረጥ እየሆነ እንደሚገኝ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ተገልጿል።
Previous Next

ፈደራል የገንዘብ ሚኒስቴር ምንስትር ክቡር በአቶ አህመድ ሽዴ የተመራዉ ልዑካን በሲዳማ ክልል አረንጎደ አሻራ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም መራሃግብር ላይ ሀምሌ 18/2013 ዓ.ም

አርበጎና /ያዬ ሲዳማ ኢትዮጵያ

Previous Next

ከዛሬ 4 ዓመታት ወድህ እንደ ሀጋራችንም ሆነ ክልላችን፡ በርካታ የዕድጋት፣ የአስተሳሰብ እና የህብር፡ ለውጥ የእያስተዋልን እንጋኛለን፡፡ ለውጡ፡ ለመልካም አሳቢዎች የሚያረጋጋ በተቃራኒው ለሚያስቡ የሚያቅለሽልሽ ሆኖል፡፡

Previous Next

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕረዝደንት ክቡር አቶ ደስታ ለዳሞ ከፈደራል ገንዘብ ሚኒስቴርና ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪ ከሆኑ ተቋማት በሲዳማ ክልል በአርበጎና ወረዳ በያዬ ከተማ የአረንጎደ አሻራ ችግኝ ተከላና ለአቅመ ደካሞች የቤት እድሳት ለማድረግ  ለመጡ እንግዶችን የእራት ግብዣ ፕሮግራም ላይ ተገኝተዉ መልዕክት ስያስተላልፉ፡፡

ሀምለ 17/2013 ዓ.ም

ሀዋሳ ሲዳማ ኢትዮጵያ

About Us

የሲዳማ ህዝብ፡ ከ100 ዓመታት የፓሌቲካ ትግል በኃላ፣ የቀደመ የመንግሥት፡ አስተዳደሩን በመመለስ እነሆ በዚህ በለውጥ ዘመን የለውጥ ዕይታ ይዞ፡ ሀገራችንንም፡ በተገባላት፡ ቃል ኪዳን መሠረት ፡ ዐለቷ እንዲ ፀና እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ዋጋው፡ ከፍ ያለ ነው፡፡ የኢትዮጱያ ድምቀት በመሆናችን እንኳን ደስ አለን!!

Flickr Photos

Address

address: Beside of Hawassa City Primary Court

phone (+251) 13181046

Email : snrsbof@snrsfb.gov.et

Fax(046)-220-60-84        

PostP.S.K. 485

Usefull Links

Announcement

Bid

Vacancy

Contact

 

Social Media

FaceBook

Youtube

Google Map

     WhatsApp

     Telegram