ESAP3 - IDA20 በዓለም አቀፍ ባንክ ሲተገበር ቆይቶ መንግሥት እንድመራው በመደረጉም እንኳን ደስ አለን፡፡ እንደሚታወቀው የሚዳሰስም ሆነ የማይዳስሰው ሃብት፤ ገንዘም ሆነ የሰው ልጅ ክህሎት፣ እውቀት እና ጉልበት፡ የተፈጠረው ለሰው ልጆች ጥቅም እንደውል ነው፡፡ ለህዝብ፡ ጥቅም ሲውሉም በጨለማ፣ በግርዶሽ የሚዉል፡ መሆን፡ የለባቸውም፡፡ ይልቀን አሣታፊ፣ አቃፊ፣ ግልፅ፣ ከአግለይነት የፀዳ፣ ኃላፈነት፡ በተሞላበት መሆን፡ አለባቸው፡፡ ለዚህም፤ ከህዝብና ከመንግሥት፣ የተቀበልነውን አዳራ መወጣትን ይጠይቃል፤ በተጨማሪም ከማናየው ነገር ግን በግላጭ ከሚያየን ፈጣሪ እና አብሮን፡ ከሚኖር ሂሊናችን ሊያጋጨን፡ የሚችል ተግባር መፈፀም አይገባንም፤ ይልቁን በትልቅ ጥንቃቂ፡ የሃብት፡ አስተዳደር ሥርዓታችን፡ ሊጎለብት ይገባል፡፡ ተጠያቂነትንና ጠያቂነትንም ልናበዛ ግድ ይለናል፡፡
በክልላችን ሞጋች፣ አመንኮኖያዊ፣ አግባባዊ፡ ጠያቂ ንቁ፣ የበቃ፣ የሚያበቃ፣ ነገሮችን አርቆ ተመልካች እና አመልካች ሰዎች እንዲፈጠሩ ተግተን፡ መሥራት ጊዜ የምንስጠው ጉዳይ፡ አይሆንም፡፡ እንደምታውቁት፡ ሲዳማ መንግሥት ከሆነበት ማግሥት አንሥቶ መላው፡ የክልላችን ነዋሪዎች በዓመቱ ውስጥ ምን ያክል ሃብት፡ እንደተመደበ የተመደበው ሃብት በዬትኞቹ ኘሮጀክቶች ላይ፡ እንደሚውል፤ ግልፀኝነትን ለመፈጠር እያደርግን ያለው ጥረት እንደ ቢሮአችን፡ የሚደነቅ ተግባር ነው፡፡ በESAP3፡ ኘሮጀክት ድጋፍም በተለይ በ8 ወረዳዎች እየፈፀምን ያለው ተግባር ለሌሎች ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ነው፤ በየቀበሌያቱ የሚገኙ ማህበረሰብ አቀፍ ኮሚቴዎችም የበለጠ እንዲተጉ፡ ማድረግ እንደተጠበቀ ሆኖ፡፡
የተከበራችሁ፡ የዚህ ኘሮግራም ተሣታፍዎች ሁላችሁም እንደምትረዱት የሰው ልጅ ፍላጎትና ያለን፡ ሃብት፡ ልጣጠም አይችልም፤ የአኮኖሚ ደረጃ፤ የአኗኗር ዜደአችንም የተለያየ ነው፡፡ ስለዚህ፡ አድሎኦዊነት፡ ቀርቶ፡ የምናገኛትን፡ ሃብት፡ ዜጎች በግልፅ እንዲያውቁ፤ የልማት፡ ሴክተር ኘሮጀክቶችም ዬት? መቼ? እና እንዴት፡ እንደሚፈፀሙ በጋሃድ ማሣወቅ ከራሥ ባለፈ፡ ለትውልድ ማሰብ፡ ይጠበቅብናል፡፡
በተጨማሪም የእጅ ንፅህናችንን በማጎልበት፣ ነገሮች ከመበላሸታቸው አስቀድሞ በመጠንቀቅ፤ የጠባቂነት እና ዓይን አፋርነት ቀርቶ፡ ሁሉም ዜጋ በንቃት ስለሚመደብለት ሃብት በምክናታዊነት ሽንጡን ገትሮ የሚሟገት እንዲሆን እንድናበቃው የአደራ መልዕክቴ ነው፡፡ ከአካል ጉዳተኞች፣ በህመም ምክንያትም የሚገለሉ፣ የሚዘነጉ፣ እና የሚሸማቀቁ በክልላችን እንዳይኖሩ፡ የዕይታ አድማሳችን የእናት፡ አይን እንዲሆን፡ ጥሪዬ ነው፡፡ ተጠቃሚ ዜጎቻችንም፡ ሆይ!! ለእናንተ አገልግሎት ይሰጥ ዘንድ በመንግሥታችሁ፡ የተሠሩ ቀን፡ ሲበሩ፡ ማብራት ብታዩ እንዲጠፉ መንገር፣ የተበላሹ የውሃ ተቋማትን ባያችሁ፡ ጊዜ ተባብሮ ማስተካኪል አሊያም ቢግልፅ፡ ለወረዳው አመራር እንድትጠቁሙ በየመንገዱ፡ ቆሻሻ እንዳይጣል፡ መጠንቀቅ እና ኘሮጀክቶች ከመጀመራቸው አስቀድሞ በሚደረግ፡ የተፈላጊነት ጥናቶች በቂ፡ እውቀት እንዲኖራችሁ፡ እንድትተጉ፡ አሳስባለሁ፡፡
የዚህ ኘሮግራም አስተባባሪዎች ዛሬ በ8 ወረዳዎች ባደረጋችሁት ድጋፍ፡ ለሌሎች ወረዳዎችም ትምህረት የሚሆን፡ ውጤት እያየን፡ ነው፡፡ እንደ መንግሥት matching fund እንኳን ይዘን ለማስፋፋት ልባችሁንና አእምሮአችሁን በማዋሃድ ከዚህ ወደ ቢሮአችሁ፡ ስትመለሱ፡ ቀና ምላሽ፡ እንድትሰጡና ክልላችን በዚህም ዜጎችን ሞጋች እና ብቁ ለማድረግ፡ የያዝነውን አቂም እንድምትደግፍ ጽኑእ እምነት አለኝ፡፡
የየወረዳ፡ እና የከተማ አስተዳደሪዎች ተጠቃሚዎች ከሚያዩት በላይ ህሊናና ፊጣሪ፡ ዘወትር ያየናልና በቅንነት፡ ለማገልገል፡ ከተጋነው በላይ፡ እንድትተጉ፡ ላበረታታችሁ፡ እወዳለሁ፡፡ በመጨረሻም ይህንን፡ ኘሮግራም በክልላችን እንድተገበር ለመሥራት የተመረጣችሁ PLCDዎች፡ ከሥራ ፈጠራ ማስፋፋት አኳያ፤ ለሥራው ቅልጥፍና፤ የተቋማችሁ፡ ደንብ፡ በሚያዘው መሠረት የአካባቢ ወጣቶችን ለቦጎ ፍቃዲኛ ወጣቶቻችን የሥራ ዕድል እንደምትፈጥሩ እምነቱ፡ ቢኖረኝም፡ በዚህ አጋጣሚ ለበረታታችሁ እፈልጋለሁ፡፡ በምክንያታዊነት የሚያምን ዜጋ መፈጠር አቋማችን፡ ነው!


